ክቡር ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደም በዛሬው የከሰዓት ውሏቸው የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሚሰጣቸውን የክህሎት መር ትምህርቶችን በዝርዝር በማድመጥ በውስጡ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል። በኮሌጁ ላይ ባደረጉት ጉብኝት የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አብዱልጀዋድ መሀመድ ፣ የአስተዳደሩ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶ/ር ፍቃዱ በየነን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ©️ ከንቲባ ጽ/ቤት